ኤርትራን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ እንዲፈጥሩ ሀሳብ ቀረበ

  • መለስካቸው አምሃ

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር

ኢትዮጵያን በይፋ በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ኤርትራን በመጨመር አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ ለመፍጠር መስራት አለባቸው አሉ፡፡

ኢትዮጵያን በይፋ በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ኤርትራን በመጨመር አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ ለመፍጠር መስራት አለባቸው አሉ፡፡

የኢዮጵያው ጠ/ሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በበኩላቸው የሱዳንና የኢትዮጵያ ግንኙነት ለአካባቢው ሀገሮች ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ገልፀው እነዚህ የአካባቢው ሀገሮች በአስቸኳይ ውህደት እንዲፈጥሩ አሳሰቡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ኤርትራን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ እንዲፈጥሩ ሀሳብ ቀረበ

ሁለቱ መሪዎች ትናንት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተገኝተው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫቸው በሁለትዮሽ ግንኙነታቸውና በአካባቢው ግንኙነታቸው አተኩረዋል፡፡ በሁለትዮሽ ግንኙነታቸው አኳያ በንግድ ለመተሳሰር ስምምነት መፈራረማቸውን ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

ኤርትራን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ እንዲፈጥሩ ሀሳብ ቀረበ