በምእራብ ወለጋ ጨሊያ ከተማ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ትላንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና የአካባቢዉ ህዝብ ባደረጉት ሰልፍ ላይ አንድ ተማሪ መገደሉ ሌላ በጽኑ መቁሰሉና ታዉቋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
ትላንት በጨሊያ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና የአካባቢዉ ዜጎች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ባካሄዱት ሰልፍ ላይ አንድ ተማሪ መገደሉና ሌላዉ በጽኑ መቁሰሉን ለደህነነቴ እስጋለሁ በማለት ስማቸዉ አንዳገለጥ የጠየቁ ነዋሪ በስልክ ለአፋን ኦሮሞ ባልደረባችን ናሞ ሳንዲ ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ፖሊሶችና አድማ በታኞች በጅምላ ህዝብ ላይ ከፍተዉ በርካታ ተማሪዎች ቆስለዋል ከፓሊሶቹ ሽሽት ጫካ የገቡም አሉ ብለዋል። የታሰሩ ተማሪዎችን ስም ዘርዝረዉ ቁጥራቸዉና ማንነታቸዉ ገና ያልተለዬ ሌሎችም መታሰራቸዉን ገልጸዋል።
የኦሮሚያ ፓሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ሃላፊ ሰለሞን ታደሰ በከተማዋ ሕዝባዊ ተቃዉሞ እንደነበርና ተኩስ ከያቅጣጫዉ ይሰማ እንደነበር ገልጸዉ፥ ተማሪዉ ከማን በተተኮሶ ጥይት እንደሞት እያጣራን ነዉ ብለዋል።
በዛሬዉ እለት ሰላምና መረጋጋት በከተማዉ ስፍኗል ሲሉ ለአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ባልደረባችን ነሞ ዳንዲ ገልጸዋል። ትዝታ በላቸዉ በአማርኛ ያቀርበችዉን ዘገባ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5