ለቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተሰጠው መኖሪያ ቤትና ጥቅማ ጥቅም ተወሰደ

አዲስ አበባ

መንግሥት በጡረታ ለተገለሉ የመንግሥትና የፓርቲ ባለሥልጣናት የሰጣቸውን መኖሪያ ቤትና ተሽከርካሪዎችን ማስመለስ መጀመሩና፣ ነጻ የህክምና አገልግሎት የመሳሰሉ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችም እንዲቋረጡ ማድረጉን የሃገር ውስጥ ጋዜጦች ዘግበዋል፡፡

የጠቅላይሚኒስትር ጽሕፈትቤት የፕሬስ ክፍል ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን፣ ጉዳዩ የቤቶች ኮርፖሬሽንን የሚመለከት ስለሆነ ኮርፖሬሽኑ በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ለቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተሰጠው መኖሪያ ቤትና ጥቅማ ጥቅም ተወሰደ