የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ሃገራቸው የምትገኝበትን አጠቃላይ ሁኔታ የሚዘረዝረውንና የወደፊት አቅጣጫቸውን የሚያመላክቱበትን የመጀመሪያ ንግግራቸውን ለተወካዮች ምክር ቤቱ ጥምር ጉባዔ ዛሬ ማታ ያደርጋሉ።
ፕሬዚደንቱ ለሀገር ውስጥና ለውጭውም ያላቸውን እና ገና የተጀመረውን የአውሮፓ 2018 ዓመተ ምኅረት ትልም የሚያዳምጡት በኮንግሬሱ አዳራሽ ውስጥ የሚታደሙት እንደራሴዎች ብቻ ሳይሆኑ በግዙፎቹ የቴሌቪዥን መረቦች በቀጥታ በሚተላለፉ ሥርጭቶች የመላው ዓለም ህዝብም ይከታተለዋል።
ትረምፕ ይህንን ንግግራቸውን የሚያደርጉት በሀገሪቱ የግብርና ቀረጥ ህግ ማሻሻያ ላይ ድል አጎናጽፏቸዋል የተባለ ውሣኔ በተወካዮች ምክር ቤቱ ከተላለፈላቸውና ፈርመውም የሀገሪቱ የታክስ ህግ ባደረጉት ሰሞን ቢሆንም ያለፈው ፕሬዚደንታዊ ዓመታቸው በብዙ ወጀብ እና ትርምስ የታጀበ እንደነበርም ታዛቢዎች እየተናገሩ ናቸው ።
ፕሬዚደንት ትረምፕ ባሳለፉት አንድ ዓመት ለአዲስ ፕሬዚደንት በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ የወረደ የህዝብ ተቀባይነት ያላቸው ፕሬዚደንት መሆናቸውንም የህዝብ አስተያየት ክትትል አኀዞች ያሳያሉ።
የአሜሪካ ድምፅ በዌብ ሳይቱና በፌስ ቡክ ገፆቹ የፕሬዚዳንቱን ንግግር በቀጥታ የሚያስተላልፍ ሲሆን በፕሬዚዳንቱ ንግግር ወቅት የየርዕሰ ጉዳዩን ማጠቃለያም በአማርኛው የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ያወጣል፤ ተከታተሉት።
ለተጨማሪ የተያይዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5