የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አምስተኛ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሃገራቸው በ2020 ዓ.ም. የምትገኝበትን ሁኔታ በዝርዝር የሚያብራራ ንግግር /State of the Union Address/ ለ116ኛው የተወካዮች ምክር ቤት ጥምር ጉባዔ አድርገዋል።
ዋሺንግተን፤ ዲሲ —
State of the Union
ፕሬዚዳንቱ የሃገራቸውን ሁኔታ “ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ጠንካራ ነው” ሲሉ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን ምላሽ የሰጡት የሚሺጋን ገዥ ግሬቸም ዊትመር ግን “ሃገሪቱ ጥሩ የሆነችው ለከበርቴዎች እንጂ ለባለመካከለኛ ገቢው አሜሪካዊ አይደለም” ብለዋል።
በፕሬዚዳንቱ ንግግርና ከዴሞክራቲክ ፓርቲው በተሰጠው ምላሽ ላይ ምሁራን ለአሜሪካ ድምፅ ትንታኔ ሰጥተዋል።
በሰሜን ካሮላይና ኤ ኤንድ ቲ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሣይንስ መምህር ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ እና በቴክሳስ ኮሊን ኮሌጅ የኢኮኖሚክስ መምህር ፕሮፌሰር ሞሐመድ ጣሂሮ ናቸው።
ሙሉውን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
በፕሬዚዳንት ትረምፕ ንግግር ላይ ትንታኔ