በዲፕሎማቶች ላይ የተጣለው ዕገዳ ተነሳ

  • እስክንድር ፍሬው

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

ዲፕሎማቶች “ለራሳቸው ደህንነት” ሲባል ከአዲስ አበባ 40ኪሎ ሜትር ራዲዮስ ውጭ ያለፈቃድ እንዳይንቀሳቀሱ የተጣለው ክልከላ መነሳቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትርና የአስቸኳይ ጊዜ ኮምንድ ፖስት ሴክሬታሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ እንዳሉት ክልከላው የተነሳው የሃገሪቱ የሠላምና መረጋጋት ሁኔታ እየተሻሽለ በመምጣቱ ነው፡፡

ፎቶ ፋይል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ክልከላው መነሣቱን ይፋ ያደረገው የእርምጃ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር ሁለት ይፋ ሲያደርግ ነው፡፡

​ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

በዲፕሎማቶች ላይ የተጣለው ዕገዳ ተነሳ