አቶ ታዬ ደንደአ የዋስ መብት ተከለከሉ

የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ድኤታ አቶ ታዬ ደንደአ

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ ታዬ ደንደአ የዋስ መብት ተከለከሉ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞው የሰላም ሚንስትር ድኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ያቀረቡትን የዋስትና መብት ጥያቄ ውድቅ አደረገ። አቃቤ ሕግ ካቀረበባቸዉ ክሶች ሁለቱ ውድቅ የተደረገላቸው አቶ ታዬ፣ በዛሬው ዕለት ስድስት ኪሎ ከሚገኘው የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ቀርበው የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ያቀረቡትን አቤቱታ ቀደም ሲል የልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያሳለፈውን የፍርድ ውሳኔ በማፅናት ነው ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገው።