ገንዘቤ ሬከርድ ሰበረች

  • ሰሎሞን ክፍሌ
    ቪኦኤ ዜና

የሶቺ ኦሊምፒክ ሜዳልያዎች፤ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ /ፎቶ ፋይል፤ ሁለቱ ምሥሎች ግንኙነት የላቸውም/

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በርሚንግሃም ላይ ከትናንት በስተያ በተካሄደው የቤት ውስጥ 2 ማይልስ ወይም ሦስት ሺ 200 ሜትር ሩጫ ውድድር 9 ደቂቃ ከ4.8 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች፡፡

የሶቺ ኦሊምፒክ ሜዳልያዎች፤ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ /ፎቶ ፋይል፤ ሁለቱ ምሥሎች ግንኙነት የላቸውም/

Your browser doesn’t support HTML5

ገንዘቤ ሬከርድ ሰበረች

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በርሚንግሃም ላይ ከትናንት በስተያ በተካሄደው የቤት ውስጥ 2 ማይልስ ወይም ሦስት ሺ 200 ሜትር ሩጫ ውድድር 9 ደቂቃ ከ4.8 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች፡፡

የ23 ዓመቷ አትሌት በሁለት ሣምንት ጊዜ ውስጥ በሦስት ርቀቶች አከታትላ ክብረወሰን በመስበሯ የበርካታ መገናኛ ብዙኃንን ትኩረት አግኝታለች፡፡

በገንዘቤ የተሰበረው ክብረወሰን ተይዞ የቆየው በሃገሯ ልጅ መሠረት ደፋር የነበረ ቢሆን ገንዘቤ የቀድሞውን ወሰን ከአምስት ሰከን በላይ በሆነ ጊዜ አሻሽላለች፡፡

በበርሚንግሃሙ ውድድር ሕይወት አያሌው ገንዘቤን ተከትላ በሁለተኛነት ጨርሣለች፡፡

በቅርቡ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች የተካሄዱ አገርአቋራጭ ሩጫ ውድድሮችም አሸናፊ ነበረች ሕይወት፡፡

በርሚንግሃም ላይ በተጨማሪም በወንዶች 800 ሜትር የኢትዮጵያው መሐመድ አማን አሸንፏል፡፡

ለሌሎችም ዝርዝር የአትሌቲክና የእግር ኳስ ዘገባዎች፣ እንዲሁም የሶቺ ኦሊምፒክ ውጤቶች የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡