የሙዚቃ ጉዳይ

አንጎል እና ሙዚቃ

ሙዚቃ ያለበት፣ “ሆን ተብሎ” ሙዚቃ የሚጫወቱ እና የሚያጫውቱበት ቤት ሙዚቃ ከማይዘወትርበት እንደምን ይለያል? ሙዚቃ ቀልብን ከማዝናናት - ውጥረትን ከማርገብ ባሻገር የጥንዶችን ፍቅር ስለማለምለሙ፣ በቤተሰብ አባላት መሃል ለሚፈጠር የተሻለ መግባባት ምክኒያት ስለ መሆኑ የሚተነትን ሳይንሳዊ ጥናት ተንተርሰን “አስገራሚውን የሙዚቃ ምስጢር እና ፋይዳ!” አስመልክቶ የተጀመረ ቅንብር ተከታይ ነው - አንዱ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሙዚቃ ፋይዳ እና የውበት ቀለማት .. ሁለተኛ ቅንብር

የሙዚቃን ሳይንሳዊ፣ ሥነልቡናዊና ማህበራዊ ጥቅም በሚመለከት ከሙዚቀኛው ሄኖክ ተመስገንና ከዶ/ር ዮናስ እንዳለ ገዳ ጋር የተጀመረ ወግ ሁለተኛ ክፍልም ተከታትሎ ቀርቧል።

Your browser doesn’t support HTML5

የሄኖክ ተመስገንና ፕሮፌሰር ዮናስ እንዳለ .. የሙዚቃ ወግ .. ክፍል ሁለት

የቀደሙትን ፕሮግራሞች ያደመጡ አንድ የራዲዮ መጽሔት ተከታታይ ያደረሱን አወያይ ጥያቄ ያዘለ መልዕክትም ቦታ አግኝቷል። ከቁም ነገርም ከለዛውም እያሉ የዕረፍት ጊዜዎን ያጣጥሙ ዘንድ ተጋብዘዋል።