በስፔን በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 205 መድረሱ ተነግሯል

በምሥራቅ ስፔን በምትገኘው ቫለንቺያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ በጭቃ የተያዘ መኪና

በምሥራቅ ስፔን በምትገኘው ቫለንቺያ የሚገኙ በርካታ ከተሞችን ያጥለቀለቀው ጎርፍ፣ አንዳንድ ቦታዎችን ከኤሌክትሪክ፣ ውሃ እና ስልክ አገልግሎት ውጪ አድርጓል።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎችም በመጥፋታቸው ፍለጋው ቀጥሏል። በርካቶች በተጥለቀለቀ መኪናቸው ወይም መኪና ማቆሚያቸው ውስጥ ቀርተው ሊሆን እንደሚችል ተሰግቷል።

በርካታ መንገዶች አሁንም በተቆለሉ ተሽከርካሪዎችና ጎርፉ ይዞት በመጣው ፍርስራሽ ተዘግተዋል።

በቫለንቺያ ብቻ ባለፈው ማክሰኞ ለስምንት ሰዓታት የጣለው ዝናብ ለ 20 ወራት ከጣለው በላይ ነበር ተብሏል።

እስከ አሁን 205 አስከሬኖች መሰብሰባቸው ሲታወቅ፣ ጥራቸው በውል ያልታወቀ የጠፉ ሰዎችንም ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ባለሥልታናት አስታውቀዋል።

በጎርፉ ምክንያት መንቀሳቀስ ያልቻሉ 4ሺሕ 500 ስዎችን መታደጉን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ምኒስትር አስታውቋል።