ዛሬ በደቡብ አፍሪካ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያውያን ንብረት ወደመ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ በዛሬው ዕለት በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የውጭ ዜጎች በተለይ ናይጄሪያውያን ከሃገራችን ይውጡ የሚሉ መልዕክቶች ሲስተጋቡ ውለዋል። ከሰላማዊ ሰልፉ ጋር በተያያዘ በተነሳው ረብሻ የውጭ ዜጎች የንግድ ተቋማት ተዘርፈዋል። ከተዘረፉት የንግድ ተቋማት ውስጥ አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን እንደሆነ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ የማህበረሰብ መሪ አቶ ታምሩ አበበ ለቪኦኤ ተናግረዋል።