የጦር ሹም ሽር አደረጉ
ጁባ፣ ናይሮቢ፣ ኒው ዮርክ —
ለደቡብ ሱዳን መረጋጋት ተግባራዊ መፍትሔ ካልተሰጠ የሲቪሉ ሕዝብ ሥቃይ እንደሚበረታ የተባበሩት መንግሥታት ሠላም አስከባሪ ኃይል አዛዥ አስጠንቅቀዋል፡፡
የሃገሪቱን ፀጥታ በሚያደፈርሱና የሰላም ጥረቱን በሚያደናቅፉ ላይም ብርቱ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የመንግሥታቱ ድርጅት በተከራያቸው ጀልባዎች ላይ አፐር ናይል ግዛት ውስጥ የተከፈተውን ድንገተኛ ጥቃት ሠላም አስከባሪ ኃይሉ በብርቱ አውግዟል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የደቡብ ሱዳን መንግሥት በመንግሥትን በኃይል በመጣል ወንጀል ይፈልጋቸው የነበሩና በቁጥጥሩ ሥር በቆዩ አራት የቀድሞ ባለሥልጣናቱ ላይ ይዞት የሰነበተውን የክሥ ጉዳይ መሠረዙን አስታውቋል፡፡
የደቡብ ሱዳን የፍትሕ ሚኒስትር ፓውሊኖ ዋናዊላ ይህንን ያስታወቁት ዛሬ ከቀትር በኋላ በሰጡት ጋዜጣዋ መግለጫ መሆኑን ጁባ የምትገኘው ሪፖርተራችን ሻርልተን ዶኪ ዘግባለች፡፡
የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ሰሞኑን የተቀጣጠለውን ደም ያፋሰሰ ግጭት ተከትሎ በደቡብ ሱዳን ላይ ማዕቀብ የመጣልን አማራጭ አንስቶ እየመከረ ካለበት የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ፅ/ቤት ማርጋሬት በሽር የላከችው ዘገባ አለ፤ ሰሎሞን አባተ ያቀርበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የጦር ኃይሎች ኤታ ማዦር ሹማቸውን ጄነራል ጄምሽ ሆዝንና የወታራዊ ደኅንነት ኃላፊያቸውን ሜጀር ጄነራል ራክ ፖል ኩዎልን ከሥልጣን ማንሣታቸውን ሪፖርተራችን አንድሪው ግሪን ከጁባ ዘግቧል፡፡
በምትካቸውም የሰሜን ባህር አገረ ገዥ ፖል ማሎንግ አዋንን ኤታ ማዦር ሹም፤ ቃል አቀባያቸውን ፊሊፕ አጉየርን የወታደራዊ ደኅንነት አዛዥ አድርገው ሾመዋል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5