Your browser doesn’t support HTML5
የደቡብ ሱዳናዉያን ሰደተኞች ጉዳይ
ካለፈዉ ወር ወር ጀምሮ አስራ አምስት ሺህ የሚሆኑ ደቡብ ሱዳናዉያን የእርስ በርስ ጦርነት ሸሽተተዉ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሲሆን በከባድ ረዥም ጉዞ ምክንያት በረሃብና በዉሃ ጥም በእጅጉ የተጎዱ መሆናቸዉን ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ መስርሪያ ቤት ታዉቋል።
የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ከፍተኛ የስራ ሃላፊ Gabriel Okeitoi እንዳብራሩት ጀልባና ተሽከርካሪ በመጠቀም ወደ አንድ መቶ አስራ ሰባት ኪሎ ሜትሮች ወይንም ስልሳ ሰባት ማይሎች ርቀት ሰደተኞቹን ልክቾር ወደሚባለዉ አዲስ የስደተኞች ካምፕ አጓጉዟል።
ብዙዎቹ ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተነስተዉ እስከ አኮቦና ፓጋግ ድረስ ረጅም ርቀት ለአያሌ ቀናት በእግራቸዉ በሚያደርጉት ጉዞ የተጠሙ የተራቡ ሰለሆኑ ከፍተኛ የሰዉነት ፈሳሽ መቀነሰም እንደሚታይባቸዉ የተናገሩት በኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ፍልሰት ድርጅት ተወካይ ከተቀሩት ተባባሪ ድርጅቶች ጋር የጤና ክብካቤ እንክብካቤ እናደርግላቸዋለን ብለዋል።
ሙሉዉን ከመለስካቸዉ አመሃ ዘገባ ያድምጡ።