የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚዳንት ሪያኸ ማቻር ደጋፊ አማጽያን ወደ 550 የሚሆኑ ሰዎችን ያጠቃለለ መርማሪ ቡድን ወደ 10 የሃገሪቱ ክፍላተ-ሃገር ሊልኩ ነው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የቀድሞው የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕረዚዳንት ሪያኸ ማቻር ደጋፊ አማጽያን ወደ መዲናይቱ ጁባና ወደ 10 ሩ የሀገሪቱ ክፍላተ-ሀገር ነገ 550 የሚሆኑ ሰዎችን እንደሚልኩ አስታውቀዋል።
አማጽያኑ ይህን ያሉት እአአ ባለፈው ነሃሴ 26 ቀን ላይ የተደረሰው የሰላም ስምምነት መተግበሩንና አለመተግበሩን እንዲከታተል በኢጋድ ማለት በምስራቅ አፍሪቃ ሀገሮች የልማት ትብብር በይነ መንግስታት የተመሰረተው የጣምራ ተቆጣጣሪና ገምጋሚ ኮሚሽን ባለፈው አርብ ጁባ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ ከተሰበሰበ በኋላ ነው። አማጽያኑ ግን በስብሰባው አልተገኙም።
የደቡብ ሱዳን የሀርነት ሰራዊት አማጽያን የውጭ ጉዳይ ሃላፊ አምባሳደር ኢዝክየል ሎል ጋትኩቶ(Ezkiel Lol Gatkuoth) የሚላከው የአመጽያን ቡድን መሪ ጄኔራል ታባን ደንግ ጋይ (Taban Deng Gai) እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
“ስብሰባ አድርገን ቡድናችንን ነገ ማክሰኞ ወደ ጁባና ወደ አስሩ ክፍላተ ሃገራት ለመላክ መወሰናችንና ለናንተና ለመላው አለም ግልጽ ለማድረግ እፈልጋለሁ። ቡድኑን የሚመሩትም ዋናው ተዳራዳርያችን ጄኔራል ታባን ደንግ ጋይ (Taban Deng Gai) ናቸው” ሲሉ የአምጽያኑ አማባሳደር አስታውቀዋል። የዜና ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5