በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ሃያ አራት የሕክምና ጣቢያዎች ተዘረፉ

  • ቪኦኤ ዜና
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ታጣቂ ቡድኖች፣ ባለፈው ዓመት ከመንፈቅ ውስጥ ሃያ አራት የሕክምና መስጫ ጣቢያዎቻችንን ዘርፈውብናል፣ መንግሥት የተሻለ ጥበቃ ያድርግልን ሲሉ የሕክምና በጎ አድራጎት ድርጅቱ ድንበር የለሽ ሃኪሞች ዋና ኃላፊ ጠየቁ።

ደቡብ ሱዳን ውስጥ ታጣቂ ቡድኖች፣ ባለፈው ዓመት ከመንፈቅ ውስጥ ሃያ አራት የሕክምና መስጫ ጣቢያዎቻችንን ዘርፈውብናል፣ መንግሥት የተሻለ ጥበቃ ያድርግልን ሲሉ የሕክምና በጎ አድራጎት ድርጅቱ ድንበር የለሽ ሃኪሞች ዋና ኃላፊ ጠየቁ።

የሜዲሳን ሳን ፍሮንቲዬ /MSF/ ዓለምቀፍ ፕሬዚዳንት ጆዋን ሊዩ፣ ደቡብ ሱዳን ያሉትን የሕክምና ጣቢያዎች ይጎበኙ ሲሆን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ተወያይተዋል፡፡

“የሚያሳዝነው ተፋላሚዎቹ ወገኖች፣ የሕክምና ጣቢያዎችን መጠበቅ ሲገባቸው፣ አዘውትረው አላማ ማድረጋቸው ነው” ብለዋል።