ሳልቫ ኪርና ሪያክ ማቸር በአዲሱ የሽግግር መንግሥት ምስረታ ጉዳይ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፡-የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቃዋሚ መሪ ሪያክ ማቻር

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር እና ተቃዋሚ መሪ ሪያክ ማቻር ትናንት ሃገሪቱ መዲና ጁባ ላይ በነገ ቅዳሜ የጊዜ ገደብ አዲሱን የሽግግር መንግሥት ለማቋቋም መስማማታቸውን ይፋ አደረጉ። ሁለቱ የሽግግር መንግሥቱ ለማቋቋም ከአሁን ቀደም ያደረጉዋቸው ሙከራዎች አልተሳኩም፣ በርካታ የጊዜ ገደቦችም አሳልፈዋል።

አሁን ያለውን የሽግግር መንግሥት እንደሚበትኑ ትናንት ለጋዜጠኞች የገለጹት በስምምነቱ መሰረት አምስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ዛሬ እንደሚሾሙ አስታውቀዋል።

“ዛሬ ተቀምጠን መንግሥታቱን ለማቋቋም ተስማምተናል። በዚህ የመንግስት ምስረታ ውስጥ እንደ የብሄራዊ አንድነት የሽግግር መንግሥት እየተነጋገርን የምንቀጥልባቸው ጉዳዮች አሉ ። ለምሳሌ የጁባ የጸጥታ አጠባበቅ እና ለዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ /SPLM / የሚሰጠው ጥበቃ ላይ እንነጋገራለን የተዋሃዱት ኃይሎቻችን ሥልጠን እስከሚጠናቀቅ ድረስ የኛ ወታደሮች አጠቃላዩን የጁባን ጥበቃ እንደሚይዙ ኃላፊነት ወስጃለሁ ሲሉ ኪር አክለው አስረድተዋል።

ከፕሬዚዳንት ኪር ጎን የቆሙት ማቻር የቀሩት ችግሮች ባፋጣኝ ይፈታሉ በሚል እሳቤ በዚህ ሳምንት በሚከናወነው የአንድነት መንግስት ምስረት ላይ እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል።