በአዲስ መልክ የተደራጀው የደቡብ ሱዳን የሰላም ሥምምነት ከተፈረመ መንፈቅ ቢያልፈውም እስካሁን አንድም የፖለቲካ እስረኛ እንዳልተለቀቀ ተመድ ያወጣው አዲስ ሪፖርት አመለከተ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ሁለት ታዋቂ የመንግሥት ተቃዋሚዎች የ/ኤስፒኤልኤምአይኦ/ አባሉ አግሬይ ኢድሪ እና የሰብዓዊ መብት ጠበቃ ሳሙኤል ሉዋክ ከነበሩበት ከናይሮቢ የገቡበት ከጠፋ ቆይተዋል።
የተመድ የደቡብ ሱዳን የኤክስፐርቶች ኮሚቴ ባወጣው ሪፖርቱ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ሁለቱም ምን እንደወሰዳቸው የማውቀው ነገር የለም ማለቱን አመልክቷል።
ሃገሪቱ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች ግን ሁለቱ ተቃዋሚዎች የጠፉበት የደቡብ ሱዳንና የኬንያ መንግሥት ሥራ ነው ይላሉ።