ደቡብ ሱዳናዊያን አዲሳባ ላይ እንደገና ተቀመጡ

  • ቪኦኤ ዜና
የተቃዋሚዎቹ ዋና ተደራዳሪ ታባን ዴንግ ጋይ እና የደቡብ ሱዳን መንግሥት ዋና ተደራዳሪ ንሂያል ዴንግ ንሂያል

የተቃዋሚዎቹ ዋና ተደራዳሪ ታባን ዴንግ ጋይ እና የደቡብ ሱዳን መንግሥት ዋና ተደራዳሪ ንሂያል ዴንግ ንሂያል

የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና የተቃዋሚዎቹ ልዑካን ቡድኖች የድርድራቸውን ሁለተኛ ዙር ትናንት አዲስ አበባ ላይ በይፋ ጀምረዋል፡፡

ደቡብ ሱዳን፣ ከተሞቿና ጎረቤቶቿ

ደቡብ ሱዳን፣ ከተሞቿና ጎረቤቶቿ

Your browser doesn’t support HTML5

ደቡብ ሱዳናዊያን አዲሳባ ላይ እንደገና ተቀመጡ

የደቡብ ሱዳን መንግሥት እና የተቃዋሚዎቹ ልዑካን ቡድኖች የድርድራቸውን ሁለተኛ ዙር ትናንት አዲስ አበባ ላይ በይፋ ጀምረዋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የተጠናቀቀው ወገኖቹ በፀብ ላለመፈላለግና በደቡብ ሱዳን መንግሥት ቁጥጥር ሥር በሚገኙ የፖለቲካ እሥረኞች ዕጣ ፈንታ ላይ ተስማምተው ነበር፡፡

የአሁኑ ሁለተኛ ዙር ድርድር የሚያተኩረው ደቡብ ሱዳንን ከሣምንታት ጦርነት በኋላ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት ሊያስገቡ ይችላሉ በሚባሉ ነጥቦች ላይ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ተቋሙ - ኢጋድ ዋና አደራዳሪ ስዩም መስፍን ደቡብ ሱዳን ውስጥ ታይቷል ያሉትን የጋራ ውድቀት በማንሣት ስብሰባውን ከፍተዋል፡፡

አማፂያኑ ተቃዋሚዎች ጥያቄዎቻቸው ካልተመለሱ ከድርድሮቹ ረግጠው እንደሚወጡ አስጠንቅቀው የነበረ ቢሆንም የውጊያውን ሥር ወምንጭ ይፈትሻል፤ በሃገር ግንባታና በብሔራዊ ዕርቅ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል በሚባለው ቀጣይ ድርድር ላይ ለመሣተፍ ዝግጁነት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ