በሲዳማና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት መንሸራተት አደጋ ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ

Your browser doesn’t support HTML5

በሲዳማና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሬት መንሸራተት አደጋ ዘጠኝ ሰዎች ሞቱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን እና በሲዳማ ክልል ወንሾ ወረዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ፣ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውንና አምስት ሰዎች መጎዳታቸውን ባልሥልጣናት አስታወቁ።

የወላይታ ዞን የካዎ ኮይሻ ወረዳ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት አስተባባሪ፣ የሁለት ቤተሰብ አባላት የኾኑ ሰባት ሰዎች፣ ትላንት ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ መሞታቸውን ለቪኦኤ አረጋግጠዋል።

የሲዳማ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ወሰንየለህ ስምኦን በበኩላቸው፣ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. በሲዳማ ክልል ወንሾ ወረዳ በተከሰተ ተመሳሳይ አደጋ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ ሦስት ሰዎች ተጎድተው ሕክምና ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።