Your browser doesn’t support HTML5
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ፣ ካለፈው ሳምንት ዐርብ ጀምሮ፣ አካባቢውን ባጥለቀለቀው የኦሞ ወንዝ ሙላት ምክንያት፣ ነዋሪዎች በውኃ መከበባቸውንና ከ79ሺሕ በላይ አርብቶ አደሮችም መፈናቀላቸውን፣ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለተፈናቀሉ ዜጎች በቂ ሰብአዊ ድጋፍ አለመቅረቡንና በዘላቂነት የማቋቋም ርምጃም አለመወሰዱን ገልጿል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዳሰነች ወረዳ ተመራጭ በበኩላቸው፣ የቱርካና ሐይቅ ወደ ኋላ በመፍሰሱና የኦሞ ወንዝ በመጥለቅለቁ የአካባቢው ነዋሪ በውኃ መከበቡንና በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸው፣ አስቸኳይ የነፍስ አድን ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡