የዳሰነች ወረዳ የጎርፍ ተፈናቃዮች በቂ ርዳታ አለማግኘታቸውን ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የዳሰነች ወረዳ የጎርፍ ተፈናቃዮች በቂ ርዳታ አለማግኘታቸውን ተናገሩ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ፣ በኦሞ ወንዝ መጥለቅለቅ የተፈናቀሉ ከ79ሺሕ በላይ አርብቶ አደሮች፣ በቂ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳልቀረበላቸው፣ ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ተናገሩ።

የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፍቅረ ማርያም አይመላ፣ በቂ ድጋፍ እንዳልቀረበ አምነው፣ የተሟላ ርዳታ ለማድረስ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደኾነ አስታውቀዋል።

በጎርፍ ሙላቱ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ማግኘት በሚቻልበት ኹኔታ ላይ፣ መንግሥታዊ ካልኾኑ ድርጅቶች ጋራ እንደመከሩም፣ አክለው ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበርያ ቢሮ(UN-OCHA) እና የድርጅቱ የሕፃናት መርጃ ቢሮ(UNICEF) በተናጠል ባወጧቸው ሪፖርቶች፣ ተጎጂዎች በቂ ድጋፍ እየቀረበላቸው እንዳልኾነ ጠቅሰው፣ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲቀርብላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።