የኢኮኖሚ ማሻሻያው ጉዳቱ እንዳያመዝን መንግሥት በጥብቅ እንዲቆጣጠር ተጠየቀ

መርካቶ ገበያ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢኮኖሚ ማሻሻያው ጉዳቱ እንዳያመዝን መንግሥት በጥብቅ እንዲቆጣጠር ተጠየቀ

መንግሥት በኢኮኖሚ ማሻሻያው፣ የውጭ ምንዛሬ ግብይቱ ገበያ መር እንዲኾን ያሳለፈው ውሳኔ፣ በኅብረተሰቡ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንዳያመዝን፣ ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓት እንዲያበጅ ባለሞያዎች ጠየቁ፡፡

የዐዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ ዛሬ ዐርብ፣ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙ ባለሞያዎች፣ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ሥርዓቱ ጥቅምም ጉዳትም እንዳለው ጠቁመው፣ ትግበራው የመንግሥት ቁጥጥር እንደሚፈልግ አመልክተዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ በበኩሉ፣ በዐዲሱ የውጭ ምንዛሬ ሥርዓት ትግበራ ላይ፣ የተጠና ጣልቃ ገብነት ይኖራል፤ ብሏል፡፡