Your browser doesn’t support HTML5
በደቡብ ኢትዮጵያ ክል፣ ጋርዱላ ዞን፣ ደራሼ ወረዳ፣ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችንና የማሕበረሰባዊ ፖሊሰ አባላትን ጨምሮ 21 ሰዎች “ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በዘፈቀደ ታስረዋል” ሲሉ ቤተሰቦቻቸውና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ መጀመሪያ ከታሰሩበት የዞኑ ዋና ከተማ ጊዶሌ ወደ ሌላ አከባቢ መወሰዳቸውን የጠቀሱት የቤተሰብ አባላት የደህንነተቸው ጉዳይ እንደሚያሳስባቸውም ተናገረዋል።
‘በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ታስረዋል’ ያለው የጋርዱላ ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ዝርዝር መረጃ ከመሰጠት ተቆጥቧል፡፡