የጋርዱላ ዞን ከእገታ የተለቀቁ የቀን ሠራተኞችን መረከቡን አስታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

የጋርዱላ ዞን ከእገታ የተለቀቁ የቀን ሠራተኞችን መረከቡን አስታወቀ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋርዱላ ዞን አስተዳዳር፣ ለኅዳሴ ግድብ የደን ምንጣሮ ሥራ በመጓዝ ላይ ሳሉ፣ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በፋኖ ታጣቂዎች ለቀናት ታግተው የቆዩ 271 ሰዎችን መረከባቸውን አስታወቁ፡፡

ከእገታው ያልተመለሱ ሁለት ሰዎች መኖራቸውን የተናገሩ ቤተሰቦቻቸው እና አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ተመላሽ ታጋቾች፣ ሁኔታው ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።