የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የሩጫ ስፖርት ኮከብ ኦስካር ፒስቶሪየስ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፡- የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የሩጫ ስፖርት ኮከብ ኦስካር ፒስቶሪየስ

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የሩጫ ስፖርት ኮከብ ኦስካር ፒስቶሪየስ የሴት ጓደኛውን በመግደል ወንጀል መጀመሪያ ላይ የተሰጠው የእሥራት ፍርድ ከእጥፍ በላይ የሚረዝም አዲስ ፍርድ ተሰጥቶታል።

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ የሩጫ ስፖርት ኮከብ ኦስካር ፒስቶሪየስ የሴት ጓደኛውን በመግደል ወንጀል መጀመሪያ ላይ የተሰጠው የእሥራት ፍርድ ከእጥፍ በላይ የሚረዝም አዲስ ፍርድ ተሰጥቶታል።

የደቡብ አፍሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችሎት ዛሬ ዓርብ በሰጠው ውሳኔ እስካሁን በእሥር ያሳለፈው ጊዜ ታስቦ አሥራ ሦስት ዓመት ከአምሥት ወር እንዲታሰር ፈርዶበታል።

ዓቃቤ ሕግ የጠየቀው አሥራ አምስት ዓመት እንዲታሠር ነበር። ሁለት እግሮቹ የተቆረጡት የአካል ጉዳተኞች ኦሎምፒክ ሻምፒየን ፒስቶሪየስ ሪቫ ስቲንካምፕን በመግደሉ መጀመሪያ የተሰጠው የሥድስት ዓመት እሥራት ፍርድ በአስደንጋጭ ሁኔታ የቀለለ ነው ብሏል ።