ጆርጅ ቢዞስ በ92 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ አክትቪስትና ጠበቃ ጆርጅ ቢዞስ

ፎቶ ፋይል፦ አክትቪስትና ጠበቃ ጆርጅ ቢዞስ

ደቡብ አፍሪካዊው ፀረ-ዘረኛው ሥርዓት አክትቪስትና ጠበቃ ጆርጅ ቢዞስ በሞት ተለዩ። በተለይም የሚታወቁት የእውቁ ኔልሰን ማንዴላ ጠብቃ በመሆን ነበር።

ትውልደ ግሪክ የሆኑት ቢዞስ፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በሰደተኛነት ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሄዱ ቤተሰባቸው ገልጿል። በ92 ዓመት ዕድሜያቸው፣ በተፈጥሮ ህመም ምክንያት፣ በቤተሰባቸው ተከበው እንዳረፉ ቤተሰባቸው ዛሬ አስታውቋል።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፣ ትላንት ባወጡት መግለጫ፣ “የሃገራችን የህግ ንስር ነበሩ” ብለዋል።

እአአ በ1960ዎቹ ዓመታት፣ የትግል ወቅት ለረዥም ጊዜ በእስር ሲማቅቁ የነበሩትን ኔልሰን ማንዴላናን ጓዶቻቸውን፣ በጥብቅና ቆመውላቸዋል።

ማንዴላ ከእስር ተፈተው፣ በሃገሪቱ የመጀመርያ ጥቁር ፕሬዚዳንት በሆኑበት ወቅት፣ ከዓለም እጅግ ተራማጅ የተባለውን ህገ-መንግሥት በማርቀቀ በኩል፣ ሚና እንደነበራቸው ተገልጿል።

“ጆርጅ ቢዞዝ ለዲሞክራስያችን ስኬት፣ እጂግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ፣ የህግ ሰው ነበሩ ሲሉ፣ ፕሬዚዳንት ራማፎሳ አሞግሰዋቸዋል።

የእርሳቸው ህልፈት እንደተሰማ፣ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች እስከ ሰፊው ህዝብ ድረስ፣ ከፍተኛ የሃዘን ስሜት እንደተንጸባረቀ ተገልጿል።