የደቡብ አፍሪካ ገዢው ኤኤንሲ ፓርቲ መልዕክተኞች ቀጣዩን የፓርቲው መሪ ለመምረጥ ማልደው ድምፅ መስጠት ጀምረዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የደቡብ አፍሪካ ገዢው ኤኤንሲ ፓርቲ መልዕክተኞች ቀጣዩን የፓርቲው መሪ ለመምረጥ ማልደው ድምፅ መስጠት ጀምረዋል።
ይህ ምርጫ ታዲያ ቀጣዩ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማን እንደሚሆን ፍንጭ የሚሰጥ እንደሚሆን ብዙዎች ያምናሉ።
Your browser doesn’t support HTML5
ቁጥራቸው ወደ አምስት መቶ የሚጠጋ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲው አባላት ጆሃንስበርግ ወስጥ ድምፃቸውን ሊሰጡ የታቀደው ትናንት እሁድ እንደነበር ሆኖም ሂደቱ መዘግየቱ ነው የተገለጠው።
አዲሱ የፓርቲው መሪ በመጠነ ሰፊ የሙስና ቅሌት ተግባራት ተወንጅለው ከፓሪቲው መሪነት የሚወርዱትን ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማን ይተካሉ።
ዙማ ሃገሪቱ እኤአ በ2019 ሀገር አቀፍ ምርጫ እስከሄድ ስልታን ላይ ይቆያሉ።
ለኤኤንሲ መሪነት የቀረቡት ዕጩ ተፎካካሪዎች ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሲሪል ራማፎሳ እና ሰፊ የዲፕሎማሲ ተመክሮ ያላቸው እና ባንድ ወቅት የፕሬዚዳንቱ ባለቤት የነበሩት ንኮሳዛና ላሚኒ ዙማ ናቸው።