ዩክሬናውያን በደቡብ አፍሪካ ተቃውሞ አደረጉ

  • ቪኦኤ ዜና

በኬፕታውን ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዩክሬናውያን መልህቁን ወደጣለው የሩሲያ የጦር መርከብ ጀልባቸውን በማስጠጋት ዛሬ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

በኬፕታውን ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዩክሬናውያን መልህቁን ወደጣለው የሩሲያ የጦር መርከብ ጀልባቸውን በማስጠጋት ዛሬ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል፡፡

ዩክሬናውያኑ ተቃውሟቸውን ያሰሙት ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይናና ሩሲያ የጦር መርከቦች ልምምድ ለማድረግ በሚዘጋጁበት ወቅት ነው፡፡

በዩክሬን እየተካሄደ ያለው ጦርነት አንደኛ ዓመት በተቃረበበት ወቅት ደቡብ አፍሪካ የጦር ልምምድ ማስተናገዷ ገለልተኝነቷን ጥያቄ ውስጥ ያስገባል ሲሉ ተቺዎች በመናገር ላይ ናቸው፡፡

በአብዛኛው ሴቶች ያሉበት ስምንት ተቃዋሚዎች “ጦርነት ይቁም” የሚል መፈክር በመያዝ ወደ ሩስያው መርከብ ሲጠጉ የሩሲያ የባህር ሃይል አባላት መርከባቸው ላይ ሆነው ይመለከቷቸው ነበር፡፡

በልምምዱ በሩሲያ መርከብ ላይ የተጫነው ሃይፐርሶኒክ ሚሳዬል ለሙከራ ይተኮሳል ሲል የሩሲያ ዜና አገልግሎት አንድ ስማቸው ያልተገለጸ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ልምምዱ ከዓርብ ጀምሮ ለ10 ቀናት እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡