ደቡብ ሱዳን ውስጥ ለአምስት አመታት ያህል የእርስ በርስ ጦርነት ይካሄድ በነበረበት ወቅት በጠላትነት ይተያዩ የነበሩት ሰዎች በጦርነት የዳሸቀችውን ሃገር መልሶ ለማቋቋም እንዲቻል ሲባል አብረው በተፋፈጉ ሰፈሮች እንደሚገኙ ታውቋል። ነገር ግን በቂ ምግብ እንኳን ለማግኘት በማይችልበት ሁኔታ ላይ እንዳሉ ተዘግቧል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
አማጽያንና የመንግስት ወታደሮች የነበሩ ሴቶች የሚገኙባቸው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተባበረ የሀገሪቱ የጸጥታ ሃይል እንዲሁኑ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው። ይህ የሆነው ከሁለት አመታት ባፊት በተደረገው የሰላም ስምምነት መሰረት ሲሆን ወደ 400,000 የሚጠጉ ሰዎች ያለቁበትን ጦርነት የሚያበቃ ተግባር ተደርጎ ታይቷል።
ሰልጣኞቹ ባሉባቸው ሰፈሮች ያለው የምግብ አቅርቦት ሊበላ የሚችልበት ጊዜ ያለፈበት ከመሆኑም በላይ በሙስና ተግባር እንደሚሰረቅ የግል ንጽሕናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ አቅርቦቶች እንደሌሉ ተዘግቧል።
አንዳንድ ሰልጣኝ ሴቶች በአከባቢው በሚገኙ ማህበረሰቦች ስራ ፍለጋ ሲወጡ አብረዋቸው በሚሰለጥኑ ወንዶች ሳይቀር አስገድዶ የመድፈር አደጋ ሊገጥማቸው ስለሚችል ከስፈሮቹ ርቀው ለመሄድ እንደሚቸገሩ ተዘግቧል።