የደቡብ አፍሪካ ት/ቤቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ሊዘጉ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ደቡብ አፍሪካ አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ለቀጣዩ አንድ ወር ዝግ እንደሚሆኑ ተገለፀ። የዘንድሮ የ2020 የትምህርት ዘመን ወደቀጣዩ 2021 እንዲገፋ ይደረጋል።

ደቡብ አፍሪካ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በርትቶባት የኮሮናቫይረስ ተጋላጮቿ ብዛት ከ4መቶ ሽህ አልፏል፤ በተጠቂዎቹ ብዛት ቀዳሚዋን ዩናይትድ ስቴትስን ከዚያም ብራዚል ህንድና ሩስያን በአምስተኛነት ትከተላለች።

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ የወሰዱትን ውሳኔ የሃገሪቱ የመምህራን ማኅበራት ተስማምተውበታል።