ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ሥልጣን ከያዙ በኋላ ሁለተኛቸው፣ በሁለቱ ፓርቲዎች መቀመጫ ብዛት ከተከፋፈለ ወዲህ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ፊት ሆነው ባሰሙት ዓመታዊ ንግግራቸው የአንድነት ጥሪ አሰምተዋል።
እየቀነሰ ስለ መጣው የሥራ አጥ ቁጥር እና በወረሽኙ የድንገተኛ ጊዜ የመከላከል ሥራዎች ማብቃቱን አስታውሰው የአብረን እንስራ ተማጽኖ ያለበት ንግግር አሰምተዋል፡፡
አብላጫ ቁጥር ባላው የተወካዮች ምክር ቤት ብዙም ያልተጠበቀ መሆኑን ጠቅሳ የዋይት ሃውሷ ዘጋቢያችን ፓትሲ ዊዳስኩዋራ ያጠናቀረችውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።