አሸባሪው ቡድን አልሻባብ ጥቃት ለማድረስ በመዛቱ፣ አሜሪካውያን ወደ ኬንያና ሶማልያ ድንበር አካባቢ እንዳይጓዙ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
አሸባሪው ቡድን አልሻባብ ጥቃት ለማድረስ በመዛቱ፣ አሜሪካውያን ወደ ኬንያና ሶማልያ ድንበር አካባቢ እንዳይጓዙ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
በተጨማሪም፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች በመላ አገሪቱ ሊደርስ ከሚችለው ጥቃት ራሳቸውን እንዲጠብቁም አስጠንቅቋል።
በዚሁ መሠረት ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ሰሜናዊ ምሥራቅ የኬንያ ውስጥ ወደሚገኙት ማንዲራ ዋጂ እና ጋሪሳ ቀበሌዎች፣ ወደ ጣና ባሕርና ላሙ የወደብ ከተሞች፣ ወደ ሰሜናዊ ማይንዲ እና ኪሊፊ ክልሎች፣ ወደ ናይሮቢ የኢሲሊ አጎራባች ክልሎች ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።
ሞምባሳ ውስጥ ከሆነ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ቀን ቀን Old Town ውስጥ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ኤምበሲው ጨምሮ አስታውቋል።