አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀገራቸውን ከጉዞ እገዳ ዝርዝር አስፋቃለሁ አሉ

  • ቪኦኤ ዜና

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሞሃመድ ኣብዱላሂ

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሞሃመድ ኣብዱላሂ የሀገራቸውን ስም ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የጉዞ እገዳ ዝርዝር ላይ ለማስፋቅ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታወቁ።

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሞሃመድ ኣብዱላሂ የሀገራቸውን ስም ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የጉዞ እገዳ ዝርዝር ላይ ለማስፋቅ ጥረት እንደሚያደርጉ አስታወቁ።

"ፋርማጆ" በሚባለው ቅጽል ስማቸው ይበልጥ የሚታወቁት ፕሬዚደንት መሃመድ አብዱላሂ ከሶማሊኛ አገልግሎት ባልደረባችን ፋላስቲን ኢማን ጋር በደረጉት ቃለ ምልልስ ሶማሌዎች ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ልጆቻቸውን እያሳደጉ የሚኖሩ ጥሩና ታታሪ መሆናቸውን ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትና መንግሥት ለማድረስ ጥረት እናደርጋለን፤ ፖሊሲያቸውን ቀይረው ሶማሊያን ከዚያ መዝገብ ሊያወጡዋት ይችሉ እንደሆን እናያለን” ብለዋል።

የሶማሊያ ፀጥታና ከፊታቸው የተደቀነው ሰብዓዊ ቀውስ ቅድሚያ ትኩረታቸው እንደሚሆን አዲሱ ፕሬዚደንት ገልፀዋል።

የፕሬዚዳንት ሞሐመድ አብዱላሂን ቃለ-ምልልስና ትንታኔ የያዘ ዘገባ በአብይ ርዕስ ይዘናል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀገራቸውን ከጉዞ እገዳ ዝርዝር አስፋቃለሁ አሉ