የሶማሊያ ፕሬዚደንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ በፖለቲካ መድረኩ ስማቸው አዲስ የሆነውን መሃመድ ሁሴን ሮብሌን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል
ሮብሌ የተሾሙት በፓርላማው ውሳኔ ከከሁለት ወራት በፊት ከስልጣን የተነሱትን የቀደሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን አሊ ኻይሬን እንዲተኩ ነው
ሮብሌ የተሾሙት ፕሬዚደንቱና አምስቱ የክልል አመራሮች በተከለሰው የምርጫ አፈጻጸም ደንብ ዙሪያ ተነጋግረው ዐለም አቀፉም ማህበረሰብ ጫና አሳድሮ ከስምምነት ከደረሱ በኋላ መሆኑ ታውቁዋል
በሶማሊያ የፖለቲካ መድረክ ስማቸው ዕንግዳ የሆነው የሃምሳ ሰባት ዓመቱ ሮብሌ ከሶማሊያ ብሄራዊ ዩንቨርስቲ በሲቪል ምህንድስና የተመረቁ መሆናቸው ተነግሯል