የሶማሊያ ምርጫ አንድ ወር ቀረው

  • ቆንጂት ታየ

ፎቶ ፋይል - ሞቃዲሾ

የዩናይትድ ስቴስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የዓለምን ትኩረት እንደሳበ ቢታመንም አፍሪካ ቀንድ ውስጥ በምትገኝ አገርም ወቅቱ የፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚካሄድበት ነው - በሶማሊያ፡፡

ሶማሊያ በመጭው ኅዳር ወር ማብቂያ ላይ ፕሬዘዳንቷንና የምክር ቤት አባሎቿን ለመምረጥ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።

እስካሁን አጠቃላይ የምርጫዎቹ ሂደት መልካም መሆኑን፣ የምክር ቤት አባል የሆኑት አብዲዋሊ ቋንያሬ ገልጸዋል።

“በየትኛውም ዓለም በሰለጠኑትም ቢሆን ምርጫ በሚካሄበት ጊዜ ቅሬታ የሚያሰሙና ምርጫው ትክክል አይደለም የሚሉ ወገኖች መኖራቸው የሚታወቅ ቢሆንም የእስከ አሁኑ የእኛ አካሄድ ግን ሰላማዊ ነው” ሲሉ የምክር ቤት አባል ቋንያሬ አክለው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሊያ ምርጫ አንድ ወር ቀረው