የሶማሊያ ፓርላማ ቃለ - መሃላ ፈፀመ

  • ቪኦኤ ዜና

ዩሩብ አህመድ ራቢ - የሶማሊያ ተመራጭ እንደራሴ /ፎቶ ፋይል/

ዛሬ ቃለ - መሃላ የፈፀሙት 281 የፓርላማ የሕግ መወሰኛና የሕግ መምሪያ አባላት የሆኑ እንደራሴዎች ናቸው፡፡

ይህ ዛሬ ወደሥራ የገባው የሕዝብ ሸንጎ ካለፈው የተሻለ ነው ብለው እንደሚያስቡ የምሥራቅ አካባቢ ጉዳዮች ተንታኝ የሆኑት አብዲዋሃብ ሼህ አብዲሰምድ ተናግረዋል፡፡

“የዛሬው ክንዋኔ በትክክለኛው አቅጣጫ የተንቀሳቀሱበት አንድ እርምጃ ነው፡፡ ሶማሊያ ወደ አዲ ዘመን ወደ አዲስ ምዕራፍ እየመራች ነው፡፡ ከዛሬዎቹ እንደራሴዎች አርባ አምስት ከመቶ የሚሆኑት ነባር የፓርላማ አባላት ናቸው፡፡ ሃምሳ አምስት ከመቶ የሚሆኑት ደግሞ አዳዲስ፣ ወጣት ንቁና የተማሪ ሰዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከአዳዲሶቹ መካከል ደግሞ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ጥሩ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ናቸው፡፡”

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሊያ ፓርላማ ቃለ - መሃላ ፈፀመ