በሶማሊያዋ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ካምፕ በወታደሮች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በሶማሊያዋ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች በተጠለሉበት ካምፕ በወታደሮች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ እስካሁን በታወቀው ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተዘግቧል።
የአይን አማኞች እንደገለጹት፥ የተኩስ ልውውጡ የተሰማው ተፈናቃዮች የምግብ እርዳታ መቀበያ ካርድ ለመውሰድ ተሰልፈው በመጠባበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው።
የመጠለያ ካምፑ ነዋሪ የሆነች ሃቢባ አብዲራህማን የተባለች አንዲት ተፈናቃይ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጠችው ቃል ወታደሮቹ ተፈናቃዩን ወደ ሰልፉ በማስጠጋት ላይ ሳሉ ነው፤ ጠብ መንጃ እስከማስነሳት የደረሰው ብጥብጥ የተቀሰቀሰው።
አንድ የሞቃዲሾው የመዲያ ሆስፒታል ሠራተኛ እንዳስረዱት ከሟቶቹ የዘጠኝ ወር ጨቅላና የሰማኒያ አምስት ዓመት እድሜ ባለ ዘጸጋ ጸጋ አዛውንት ይገኙበታል።
በተኩስ ልውውጡ ሌሎች ቁጥራቸው አሥር የሚደርስ ሰዎች መቁሰላቸውንም ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት ውስጥ በተከታታይ አካባቢውን ተመታው ድርቅና ለዓመታት የዘለቀው ብጥብጥ በብዙ ሚልዮኖች የሚገመቱ ሶማሊያውያንን በእርዳታ እህል ጥገኛ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ዘገባውን ከዚህ በታች ካለው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5