ሞቃዲሾ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ የሰው ህይወት አለፈ

  • ቪኦኤ ዜና
ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ ዛሬ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ፣ በትንሹ 17 ሰዎች መሞታቸውን የሐኪም ቤት ምንጮች ለቪኦኤ ገለፁ።

የሞቃዲሾ ትልቁ ሆስፒታል ዳይሬክተር ዶ/ር ሞሓመድ ዩሱፍ እንደገለፁት፣ ሌሎች 28 ቁስለኞች ሐኪም ቤት ገብተዋል።

አደጋው የደረሰው አንድ ተጠርጣሪ አጥፍቶ ጠፊ፣ ይጓዝባት የነበረችውን ተሽከርካሪ፣ ሕዝብ በሚበዛበት የሞቃዲሾ አውራ-ጎዳና መጋጠሚያ ላይ በማፈንዳቱ እንደሆነም ተገልጿል። ለፍንዳታው አል-ሻባብ ኃላፊነት መውሰዱንም አስታውቋል።