በሶማልያ የታችኛው ሸበሌ ክፍለ ሃገር በባራዌ ከተማ ዛሬ በኳስ ጨዋታ ሥፍራ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ በትንሹ አራት ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ የፀጥታ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ሌሎች አሥራ ሦስት መቁሰላቸውም ተነግሯል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በሶማልያ የታችኛው ሸበሌ ክፍለ ሃገር በባራዌ ከተማ ዛሬ በኳስ ጨዋታ ሥፍራ ላይ በደረሰ የቦምብ ፍንዳታ በትንሹ አራት ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ የፀጥታ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ሌሎች አሥራ ሦስት መቁሰላቸውም ተነግሯል።
ከርቀት የሚቆጣጠሩት ቦምብ የፈነዳው ባራዌ ከተማ ውስጥ ለዋንጫ የሚደረግ የግማሽ ፍፃሜ ግጥሚያ ላይ ነው።
ከተማይቱ ከሞቃዲሾ ደቡብ ምዕራብ 220 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።
ቦምቡ ተደብቆ የነበረው የከተማይቱን ባልሥልጣናት ለይቶ ለመምታት በታቀደ በልዩ መቀመጫዎች ሥር እንደነበርና ባልሥልጣናቱ ግን ባደረባቸው ጥርጣሬ ምክንያት ሌላ ሥፍራ መቀመጣቸው ተዘግቧል። እናም ፈንጂው አንዳንድ ተጫዋቾችና ተመልካቾችን ጎድቷል ተብሏል።