ሶማልያ ውስጥ በተካሄደ ጥቃት የሃያ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ተገለጸ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ዛሬ የተካሄደው ጥቃት፣ ሕዝብ በሚበዛበት በአንድ የሞቃዲሾ አውራ መንገድ ላይ ሁለት ተሽከርካሪዎች የቦምብ ፍንዳታ ባደረሱ ማግስት ነው።
በነውጠኞችና በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መካከል በተካሄደው ጥቃት፣ ከሞቱት በተጨማሪ፣አርባ ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል።
ከአል ቃዒዳ ጋር የሚሰራው አል ሻባብ ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱም ተገልጧል። አንድ የአል ሻባብ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ዜና አውታር በሰጠው ቃል፣ ቡድኑ ማካ አልሙካራማህ ሆቴልን መቆጣጠሩን ገልፃል። ቃል አቀባዩ አበዲሲሲ አቡ ሙሳብ በሰጠው ገለፃ፣ የመንግሥት ኃይሎች ወደ ሆቴሉ ለመግባት ሦስት ጊዜ ሞክረው ተዋጊዎቹ እንዳላስገቧቸውና አሁንም በቡድኑ ቁጥጥር ሥር እንደሚገኝ አመልክቷል።