የሞቅዲሾ ፍንዳታ በሀገሪቱ የሽብር ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተገለፀ

ባለፈው ቅዳሜ ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ የደረሰው ፍንዳታ፣ በሀገሪቱ የሽብር ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተገለፀ።

ባለፈው ቅዳሜ ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ የደረሰው ፍንዳታ፣ በሀገሪቱ የሽብር ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተገለፀ። ነዋሪዎች በጥቃቱ የተሰማቸውን ቁጣ ለመግለፅ፣ ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውም ታውቋል፣

ዩናይትድ ስቴትስም ጥቃቱን ማውገዛ ታውቋል።

በቅዳሜው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 276 መድረሱን፣ የቆሰሉት ደግሞ 429 እንደሆኑ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አብድራህማን ኦስማን ገልፀዋል፡፡

በትናንቱ ዕለት፣ ጥቃቱ በደረሰበት ስፍራ የተሰባሰበው ሕዝብ፣ ሽብርተኞችን በማውገዝ ቁጣውን በከፍተኛ ስሜት ገልጿል። አንዳንዶቹም፣ በስፍራው ደርሰው ሁኔታውን ሲመለከቱ አልቅሰዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የሞቅዲሾ ፍንዳታ በሀገሪቱ የሽብር ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተገለፀ