አልሻባብ ባካሄደው ጥቃት የሶማልያ ወታደሮች መገደላቸው ተገለፀ

  • ቪኦኤ ዜና
አንድ የሶማልያ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሰጡት ገለፃ፣ ሁለት የሶማልያ ወታደሮችና አሥራ ሁለት ነውጠኞች፣ አልሻባብ ባካሄደው ጥቃት ዛሬ አርብ መገደላቸው ታውቋል።

አንድ የሶማልያ ከፍተኛ ባለሥልጣን በሰጡት ገለፃ፣ ሁለት የሶማልያ ወታደሮችና አሥራ ሁለት ነውጠኞች፣ አልሻባብ ባካሄደው ጥቃት ዛሬ አርብ መገደላቸው ታውቋል።

ነውጠኞቹ የሂራን ክልል አስተዳዳዲ በሚሄዱበት መኪና ላይ ነው የደፈጣ ውጊያ ከፍተው ግድያን የፈፀሙት።

አስተዳዳሪው አሊ ጄይቴ ኦስማን እና ሌሎች ወታደራዊ ባለሥልጣናት ከአደጋው እንዳመለጡና፣ ጥቃቱ የተኬደውም ከቤሌድዊን በስተሰሜን 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሆነ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከአል ቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለው የአልሻባብ ተዋጊዎች፣ ወደ ሶማሌላንዷ ፑንትላንድ እያፈገፈጉ መሆናቸው ተገለፀ።