የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከቪኦኤ ጋር

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

የሶማሌ ክልል አስተማማኝ ሰላም እንዳሰፈነና የፌዴራል መንግሥትንም በሚጠበቅበት ሁሉ ለመደገፍ ዝግጁ እንደሆነ አስታወቀ። የክልሉ ተጠባባቂ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “በትግራይ ክልል እየተወሰደ ነው” ያሉት ህግን የማስከበር ዘመቻ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

የትግራይ ክልል የድርድር ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት ህገመንግሥቱን በመጣስ ያካሄደውን ምርጫ ውድቅ ማድረግ፣ በውስጡ የደበቃቸውን ወንጀለኞች አሳልፎ መስጠትና ለሰላም ዝግጁ መሆኑን ማረጋገጥ ነበረበት ያሉት አቶ ሙስጠፌ ይህ ህግን የማስከበር እርምጃ እንጂ ዓለም አቀፍ ድርድር አያስፈልገውም ብለዋል። ሁሉም ክልሎች የትግራይ ክልል ተወላጆችን መብት ያላግባብ እንዳይጥሱ አቅጣጫ እንደተቀመጠላቸውም አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ከቪኦኤ ጋር