ድሬዳዋ —
የሶማሌ ክልል መንግሥት የአፋር ልዩ ኃይልና ኡጉጉማ የተባሉ የአፋር ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ከ350 በላይ ሰዎች እንደተገደሉ አስታወቀ። የአፋር ክልል በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ምላሽ ባይሰጥም በክልሉ የመንግሥት መዋቅር የሚሠሩ ግለሰቦች ግን ኡጉጉማም ሆነ የአፋር ልዩ ሃይል የተባለውን ጥቃት አልፈጸመም ብለዋል።
የይገባኛል ጥያቄ ከሚነሳባቸው ሦስት ከተሞች አንዷ በሆነችው፤ የሶማሌ ክልል ገርበኢሴና የአፋር ክልል ደግሞ ገዳማይቱ እያሉ በሚጠሩት ቦታ ላይ ተፈጸመ በተባለው ጥቃት አብዛኞቹ ተጎጂዎች የሶማሌ ሴቶችና ህጻናት ናቸው ተብሏል።
ለጥቃቱ የፌደራል የጸጥታ ኃይሎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አለመወጣታቸው ነው ሲል የከሰሰው የሶማሌ ክልል፣ በከተማዋም ከፍተኛ ውድመትና ዘረፋ ተፈጽሟል ብሏል። ጥቃቱ አልተፈፀመም ሲሉ ማስተባበያውን የሰጡት በአፋር የመንግሥት መዋቅር የሚሠሩ ግለሰቦች እንደተናገሩት፣ ይልቁንም አጋጣሚውን በመጠቀም የክልል ልዩ ኃይል ሊይዛቸው የማይችላቸውን ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም በአፋር ክልል ላይ ዛሬ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5