የአስቸኳይ ጊዜ ታሳሪዎች በደብዳቤ አቤቱታ አቀረቡ

Your browser doesn’t support HTML5

የአስቸኳይ ጊዜ ታሳሪዎች በደብዳቤ አቤቱታ አቀረቡ

የሕዝብ ተወካዮችን ጨምሮ በአስቸኳይ ዐዋጁ የታሰሩ 14 ሰዎች “አካላዊ፣ ሞራላዊ እና ሥነ ልቡናዊ ጥቃት እየተፈጸመብን ነው” አሉ “በእገታ ላይ ነን” ያሉት ተጠርጣሪዎቹ፣ “ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት” ሰለባ እንደሆኑና ለፍትሕ ሳይቀርቡ ከሰባት ወራት በላይ መቆየታቸውን፣ ለተለያዩ አካላት በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡን የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ ተጠርጣሪዎችን ለተራዘመ ጊዜ ያለፍርድ በእስር ማቆየት የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን እንደሚያስከትል ገልጸዋል፡፡

ከመብቶች ጥሰት ጋራ በተገናኘ የሚነሡ ቅሬታዎችን፣ በምክር ቤት ኃላፊነት የተሰጠው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መርማሪ ቦርድ በትኩረት ሊከታተል እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በታሳሪዎቹ የቅሬታ ደብዳቤ ላይ፣ ከቦርዱ እና ከመንግሥት አካላት አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።