ደኢህዴን የሥራ ኃላፊዎችን ማገዱን አስታወቀ

በሀዋሳ ከተማና በክልሉ ተፈጥሮ ከነበረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የደቡብ ኢትዮጲያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ደኢህዴን ) የስራ ሃላፊዎችን ማገዱን አስታወቀ።

ከስልጣን የማንሳት አገዳ የጣለባቸው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፣ የሲዳማና የሀድያ ዞን መስተዳድር የፊት አመራሮች መሆናቸውን ንቅናቄው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
ድርጅቱ ከስልጣን አግጃቸዋለሁ ያላቸውን ባለስልጣናት ሆነ መጠናቸውንና ማንነታቸውን በስም ከመግለፅ ተቆጥቧል ።
በሌላ በኩል ድርጅቱ ከከፍተኛና መካከለኛ አመራሮቹ ጋር በሀዋሳ ከተማ ዛሬ መምከር ጀምሯል።

ተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ደኢህዴን የሥራ ኃላፊዎችን ማገዱን አስታወቀ