ሀዋሳ —
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ውሳኔ ህዝብ እንዲራዘም መወሰኑን የዳውሮ ዞን፣ የኮንታ ልዩ ወረዳ አስተዳደር የምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር እና የውሳኔ ህዝብ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተቃወሙ።
የድምፅ መስጫው ቀን ተራዝሟል መባሉ ያልታሰበ እና ዱብዳ ነገር በመሆኑ በህዝብ ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩን ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩት የአካባቢው የመንግሥት አካላት፣ ምርጫው ቀድሞ ሲል በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲከናወንም አሳስበዋል።
ውሳኔ ህዝበ በሚከናውንባቸው ምርጫ ክልሎች በጸጥታ ችግር የተነሳ ድምጽ የማይሰጥባቸው ምርጫ ክልሎች በመኖራቸው ህዝበ ውሳኔው ከሌሎች የምርጫ ክልሎች ጋር ጷግሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ይከናወናል የሚል ውሳኔ ማስተላለፉ ተዘግቧል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5