በስልጤ ዞን ወረቤ ከተማ እና በሳንኩራ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት አምስት አብያተ ክርሲቲያናት መቃጠላቸው ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በስልጤ ዞን ወረቤ ከተማ እና በሳንኩራ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት አምስት አብያተ ክርሲቲያናት መቃጠላቸው ተገለፀ

ትናንት እና ዛሬ በስልጤ ዞን ወረቤ ከተማ እና በሳንኩራ ወረዳ በተፈፀመ ጥቃት አምስት አብያተ ክርሲቲያናት ለቃጠሎ መዳረጋቸውን እና ካህናትም ጉዳት እንደደረሰባቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስስቶያን የሃዲያ እና የስልጤ ዞኖች አገረስብከት ሥራ አስኪያጅ መላከ ህይወት ቀስስ ንጉሴ ባወቀ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ ።

ጥቃቱን ለማስቆም ከሞከሩ ተማሪዎች መካከል ሦስት ተማሪዎች መገደላቸውንና ፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ደግሞ ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸውን ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሐመድ አወል በበኩላቸው በጥቃቱ ህይወቱ ያለፈው አንድ ተማሪ ብቻ መሆኑን እና እሱም ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ መላኩን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።

በአብያተ ክርሰቲያት እና በተማሪዎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ በተዋረድ ካሉ የመንግሥት አካላት ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትም ሆነ ከቅዱስ ሲኖዶስ የወጣ መግለጫም የለም። የደቡብ ክልል መንግሥት ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ኃይማኖትን ሽፋን በማድረግ በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ እና በሳንኩራ ወረዳዎች የተፈፀመውን ጥቃት እንደማይታገስ አስታወቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ