የአዲሱ የሲዳማ ክልል መግለጫ

ሀዋሳ

አዲሱ የሲዳማ ክልል ሃገር ለማተራመስ ለሚጣጣሩ አካላት እድል እንደማይሰጥና ከፌዴራል መንግሥት ጎን በመቆም ለኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና እንደሚሠራ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ አስታውቋል።

በዚህ ክረምት በአገረ አቀፍ ደረጃ ለመትከል ከታቀደው 5 ቢሊዮን ችግኝ ክልሉ በአንድ ጅምበር 11 ሚሊዮን ችግኝ መተከሉንና እስከ ሃምሌ 30 / 2012 ዓም 215 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተከል የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ አስተውቀዋል።

ፓርቲው ትናንት ባወጣው መግለጫ ክልሉ ከመሠረተ ወዲህ ለ145 ሺህ ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አመልክቷል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የአዲሱ የሲዳማ ክልል መግለጫ