ለዓመታት የኖሩበት ቤት እየፈረሰባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

ለዓመታት የኖሩበት ቤት እየፈረሰባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

ሸገር ከተማ በሚል እንደ አዲስ እየተዋቀረ በሚገኘው ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ስር በሚገኙ አካባቢዎች ለዓመታት መኖራቸውን የጠቀሱ ነዋሪዎች ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ቤታቸው እየፈረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በደረሰባቸው በደል ማዘናቸውን የገለፁ የገጣፎ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች፣ አግባብ ባልሆነና ብሔርን በለየ አካሄድ ያለምንም ማስጠንቀቂያ መንግሥት ቤታቸውን እንዳፈረሰባቸው ተናግረዋል። “በዚህም ምክኒያት ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል” ብለዋል።

ስለጉዳዩ የተጠየቁት የሸገር ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ “እያፈረስን ያለነው የግንባታ ፈቃድ የሌላቸውን ነው” ብለዋል፡፡ ብሔርን የለየ ቤት ማፍረስ እንዳልተደረገ የገለፁት ዶ/ር ተሾመ ቤቶቹ ከመፍረሳቸው በፊት በቅድሚያ ከነዋሪዎቹ ጋር ውይይት እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

በሸገር ከተማ ስላለው የቤቶች ፈረሳ ጉዳይ መግለጫ ያወጣው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በበኩሉ ለነዋሪዎቹ ምትክ ሥፍራ ወይም ጊዜያዊ ማቆያ ሥፍራ ሳይዘጋጅ ቤታቸው መፍረሱ ተገቢነት የሌለው መሆኑን ገልፆ፣ አንዳንዶቹ ፈረሳዎች የሕግ ሥነ ሥርዓትን ያልተከተሉና ከመንግሥት በኩል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ የታከለባቸው ናቸው ብሏል።

የዘገባውን ሙሉ ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።